ኦቶሜትድ ቴለር ማሽን



የማህበረሰቡን የገንዘብ አጠቃቀም አቅርቦት ለማገልገል የተፈበረከ ማሽን ሲሆን በተዘረጋለት የአውታረመረበረ (Network) መሰመር አማክኝነት በባንኩ አቅራቢያ፣ ግሮሰሪ አካባቢ፣ የገበያዎች ዙሪያ፣ የአዳራሽ ሱቆች እንዲሁም የጋዝ ማደያዎች አጠገብ በመትከል ደንበኞች በቀላሉ ከሚያጠራቅሙት ሒሳብ ላይ እንዲወስዱ የሚያደርግ የገንዘብ ከፋይ ማሽን ነው፡፡ ማሽኑን በመጠቀም ገንዘባቸውን ለማውጣት፣ ተቀማጭቸውን ለማወቅ፣ የገንዘብ ዝውውር ለማድረግ እና ሌሎች አገልግሎቶች በመስጠት ይታወቃል፡ የተወሰኑት ማሽኖች መዳሰሻ (Touch Screen) ማሳያዎችን የሚጠቀሙ ሲሆን አብዛኞቹ ደግሞ የፊደል ሰሌዳውን (Keyboard) ይጠቀሙበታል፡፡ የሒሳቡ ባለቤቶች ገንዘባቸውን ለመጠቀም ባንኩ የሰጣቸውን የፕላስቲክ ካርድ ወደ መክተቻው ወይም ማግሰተራይፕ ካስገቡ ቦኃላ ማሽኑ የሚጠይቃቸውን የማለፊያ  ቁልፍ (Password) በመጠቀም ተቀማጭ ገንዘባቸውን መቁጠር ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ተጠቃሚው ጉዳዩን ከጨረሰ ቦኃላ ማሽኑ የሚሰጠውን ሪሲት በመውስ በባንኩ ካለው ቀሪ ሒሳብ ጋር ሊያመሳክርበት ይችላል፡፡

No comments: