ወደ
ጂ-ሜይል መለያ ሳጥናችን ለመግባት የሚያገለግሉ የመግብያ ቁልፎችን ሰብሮ (Hacking) በመግባት በቀላሉ ለመበርበርና መረጃዎችን
ለመስረቅ ያዳግታሉ:: ይኸውም በዛ ያሉ ፊደላትን እና የቁጥር አሐዞችን የሚጠቀም በመሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከአንድ ብርቱ ሁለት
መድኃኒቱ እንደሚባለው የሁለት ደረጃ (Two Step Verification) ሚስጢራዊ ኮድ ማረጋገጫዎችን መጠቀም በጣም የተሻለ ሆኖ
እናገኘዋለን፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው የእኛን የመግቢያ ስም (User Name) እና የመግቢያ ቁልፍ (Password) ሰርቆ ቢገኝ
እንዲሁም ለመጠቀም ቢሞክር ከመደበኛው የሚስጢር ቁልፍ ባሻገር በተጨማሪ በሞባይል ስልክ ቁጥራችን የሚላክ ስውር ቁጥር መጠቀም ስለሚያስፈልገው
ሌብነቱ ከንቱ ይሆንበታል፡፡ ቀሪውን ከመጽሐፉ ያገኛሉ
No comments:
Post a Comment