ጃቫ በሰን ማይክሮሲሰተም ካምፓኒ አማከኝነት የለማ (Developed) ኦብጀክት ኦሬንትድ የኮምፒዩተር ቋንቋ ፍርግም (Program) ሲሆን አልሚዎቹ ሶፍተዌሩን ተጠቅመው መስራት ሲጅምሩ ከማሽን ጥገኝነት ውጭ በሆነ መልኩ የራሱን ባይትኮድ (Byte Code) ይጠቀማል፡፡ ማለትም ጂት (JIT) በተባለው መጠቅለያው (Compiler) አማክኝነት ባይት ኮዱን ወደ ማሽን ኮድ ይቀይረዋል፡፡ አልሚዎቹ ለዴስክቶፕ እና አገልጋይ (Servers) ኮምፒዩተር የሚሆኑ ፍረግሞችን ለማበልፀግ ጃቫ ስታንዳርድን ይጠቀማሉ በተመሳሳይ ለስማርት ስልኮች (Smart Phone) እና የሞባይል ቀፎዎች ፍርግሞችን ለመስራት ጃቫ ማይክሮን (Java Platform, Micro Edition) ይጠቀማሉ እንዲሁም ውስብስብ የሆኑ የድር መተግበሪያዎችን (Web Application) ለመስራት ጃቫ ኢንተርፕራይዝን ይጠቀሙበታል፡፡
No comments:
Post a Comment