ኖኪያ



ወደ አራት ቢሊዮን የሚጠጋው የዓለም ህዝብ የሞባይል ቀፎዎችን እንደሚጠቀም ይገመታል፡፡ እንደ እድል ሆኖም አብዛኛው ህዝብ የኖኪያ ቴክኖሎጂዎች ባለቤት ነው፡፡ የፊኒሾች ካንፓኒ ከሌሎች ታዋቂ ብራንዶች ጋር አንድ ላይ በመሆን የአውሮፓ እና የእስያን ገብያ ተቆጣጥሮታል፡፡
እዚህ የደረሰው የኖኪያ ታሪክ እጅግ በጣም እረዥም ነው፡፡ በ1860 ፊንላንድ ኖኪያንቪርታ ወንዝ አካባቢ በፈሬድሪክ አይድስታም ኣማክኝነት ወረቀትን በማምረት የተጀመረው ካምፓኒ ስሙን ኖኪያ ብሎ በመጥራት ከመቶ አመት ቦኃላ ጎማዎችን እና ገመዶችን ወደ ማምረት ተዘዋወሮአል፡፡ ካምፓኒው በመቀጠል ትኩረቱን ወደ ኮምኒኬሽን እና ተያያዥ አገልግሎቶች ያዞረ ሲሆን የኖኪያ ሞባይል ቀፎዎችን እንዲሁም ካሜራዎችን በማምረት ግንባር ቀደም ለመሆን በቅቶኣል፡፡ በ2009 ያስተዋወቀው ኖኪያ ቡክሌት 3ጂ ኔትቡክ ቴክኖሎጂ የ12 ሰዓት አገልግሎት አቅም ያለው ባትሪ ነበረው፡፡ ኔትቡኩ 2ሴሜ እርዝመት የነበረው ከመሆኑም በተጨማሪ በዊንዶው ሥርዓተ ከዋኝ (Operating System) የሚሰራ ነበር:: እንዲሁም ዌብ ካም፤ ብሉቱዝ እና የጂፒኤስ ሪሲቨሮች ተገጥመውለታል፡፡ 

No comments: