ከአንድ
ቢሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ በየቀኑ ዓለም ዓቀፉን ድረ መረብ (Internet) ለተለያየ አገልግሎት ይጎበኘዋል ይህውም፡
Ø ከሚያውቃቸው እና ከማያውቃቸው ግለሰቦች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር
Ø ጥናታዊ ጽሁፎችን ለመስራት፣ መረጃዎችን ለማግኘት እንዲሁም ዜናዎችን ለማዳመጥ
Ø እቃዎችን ለመግዛት እና ለመሸጥ
Ø የባንክ ሥርዓቶችን ለማከናወን
(ATM) ወይንም ኢንቪስትመንቶችን ለማካሄድ
Ø የኢንተርኔት ላይ ስልጠናዎችን ለመውሰድ
ወይም የርቀት ትምህርቶችን ለመማር
Ø ሙዚቃ እና ፊልሞችን ለማውረድ
(Download)
Ø ደብዳቤዎችን ለመላላክ
(E-mail)
Ø ኮንፈረንሶችን ለማካሄድ
Ø ፍቶ እና ቪዲዮዎችን ለመለዋወጥ
Ø የድር መተግበሪያዎችን ለመጠቀም
(Web Application)
Ø ሶፍትዌሮችን ለመጫን (Run
online setup)
Ø ጌሞችን ለመጫወት (Online
Game) ወዘተ…
ከተዘረዘሩት
መካከል እንዱን ማድረግ የቻልን እንደሆነ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ነን ለማለት እንችላለን ይሁን እንጂ ስለ ኢንተርኔት ያለን እውቀት
በቂ ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡ አንዳንድ ግለሰቦች ሰለኢንተርኔት ያላቸው እውቀት ከበቂ በላይ እንደሆነ ያስባሉ እናም ስትነግሮአቸው
አውቀዋለው ይሏችኃል ይህ ግን እጅግ በጣም ጎጂ አመለካከት ነው፡፡ ፌስቡክን ከፍተን መለጠፍ ሰለቻልን (Post) ብቻ ሰለ ኢንተርኔት እናውቃለን ካልን ተሳስተናል ምክንያቱም ፌስቡክ ማለት አጠቃላይ
ኢንተርኔት ማለት ሰላልሆነ፡፡ ይልቁንም ፌስቡክ አንዱ የማህበረሰብ ድረ ገጽ ነው፡፡ ፌስቡክ በራሱ እንድ ሺህ እንድ አገልግሎቶች
አሉት ወደ ውስጥ እየዘለቃችሁ ስትገቡ ትገረማላችሁ፡፡ በይነመረብ ከሚለው መጽሐፍ አዘጋጆች መካከል አንድዋ የሆነቸው ሰርካለም ደገፉ
ባለፈው አንድ ዓመት ከስድስት ወር ውስጥ ብቻ ፌስቡክን በተመለከተ ወደ 300 ገጽ ያለው መመሪያ በሁለቱም ቋንቋዎች (አማርኛ እና
እንግሊዘኛ) ያዘጋጀች ሲሆን እሷ አንደምትለው ከሆነ እጅግ በጣም ሰፊ ነው፡፡ “እስካሁን የማውቀው 20 እጁን ብቻ ነው” ብላ ነበር፡፡
ሰለፌስቡክ
ያጋጠመኝን ነግሪያቹሁ ላብቃ መጽሐፉ ተስተካክሎ ካበቃ ቦኃላ አንድ ነገር አነበብኩ በዚህ መሰረት ፌስቡክን እየተጠቀምኩ ሳለ ያነበብኩትን
የጥበቃ ማቀናበሪያ (Security Setting) አገልግሎት ተግባራዊ አደረኩ አንድ ቀን የፌስቡክን ጉልበት አየሁት፡፡
ነገሩ እንዲህ
ሆነ፡፡ ቀኑ እሁድ 12 ስዓት ፒያሳ መካከል ከተኮለኮሉት የኢንተርኔት ካፌዎች ውስጥ በአንዱ ኢንተርኔት እየተጠቀምኩ ነው፡፡ አስቸኳይ መልእክት ሰለመጣልኝ የፌስቡክ አካውንቴን
ከፍቼው ነበር፡፡ ሆኖም መብራት በመጥፋቱ ግንኙነታችን ተቋረጠ ምንም አማራጭ አልነበረኝም፡፡ አካውንቴን እንደተከፈተ ጥየው ልሄድ
ነው ስል እንደ መጠራጠር አልኩ ምክንያቱ ደግሞ ኪፕ ሚ ሎግድ ኢን (R Keep me Logged In)
የሚለው ሳጥን ራይት መደረጉን ወይም አለመደረጉን ባለማስተዋሌ ነው:: ይህ እንኳን ባይሆን ኩኪሶች መረጃዬን ይዘውት ይሆናል ስል
ተጠራጠርኩ ነገር ግን አማራጭ አልነበረኝም ኮምፒዩተሩ የግሌ ባለመሆኑ ቅር ተሰኝሁ፡፡ በአካውንትዋ መሰረቅ ምክንያት መቶ ሺህ ብር
ክፈይ ያለዚያ ከባለሽ ጋር እናፋታሻለን የተባለችውን ልጅ እያስታወስኩ ወደ ቤቴ ሄድኩ፡፡
በነጋታው
እግረመንገዴን ወደ ካፌው አቀናሁ ሆኖም ጠዋት በመሆኑ ዝግ ሆኖ ጠበቀኝ አሁን እዚህ ድረስ መጥቶ አካውንቴን ማን ይዘጋልኛል ስል
ተነጫነጭኩ፤ አይ አይ ወዲያው ቢሮ እንደደረስኩ ፓስዋርዴን እቀይረዋለሁ ቢሰርቁኝ እንኳን ሪሴት (የኢ ሜይል አካውንትን ተጠቅሞ
ወደነበረበት መመለስ) አደርገዋለው ስል ተፅናናሁ፡፡ ቢሮ እንደገባሁ የፌስቡክ አካውንቴን ከፈትኩት የተቀየረ ነገር አልነበረም፡፡
የኢ ሜይል አካውንቴንም ከፈትኩ ለውጥ አልነበረም አዲስ ነገር ይኖራል በማለት መልዕክቶቹን ተመለከትኩ አምስተኛው መልእክት እጅግ
አስገረመኝ የፌስቡክ አካውንትዎ አደጋ ላይ ነው የሚል ነበር፡፡ እየተደነኩ ከፈትኩት የመልዕክቱ ይዘት እንዲህ ይላል በትናንትናው
ዕለት 12 ሰዓት ላይ ይህንን የኔትወርክ አድራሻ በሚጠቀም ኮምቲዩተር፤ ዊንዶው ሰበን በሚባል ኦፕረቲንግ ሲስተም ላይ፤ ሞዚላ በተባለው
ብራውዘር አማካኝነት የፌስቡክ አድራሻህን ከፍተህው ነበር እስካሁንም አልተዘጋም ሰለዚህ ዝጋው (Inactive Account) ያለበለዚያ
የሚል መልዕክት ነበር እኔ ፓስዋርድ ለመቀየር ሳስብ እንዲህ ገላገልከኝ! በድጋሚ እየተደነኩ ዘጋሁት (ልብ በሉ 6ኪሎ ሆኜ ፒያሳ
የከፈትኩትን ሰዘጋው)፡፡ መልዕክቱን የላከልኝ የፌስቡክ ሴኩሪቲ ሴቲንግ ነበር፡፡ ትዝ ሲለኝ ያኔ ያስተካከልኩት እንደሆነ አስተዋልኩ፡፡
በቀጥታ ወደ መረጃ ሥርዓት አስተዳደሩ ሄጄ ፌዝቡክ የሚለውን
የቦርድ ላይ ጽሑፍ አጠፋሁት የክፍሉ ሰራተኞች ተንጫጩብኝ ይሁን እንጂ ምክንያቱን እና ያጋጠመኝን አንድ በአንድ ነግሪያቸው ሰጨርስ
የፌስቡክ የጥበቃ መቀናበሪያ (Security Setting) ተመችቶአቸው ነበር፡፡
በይነመረብ
(የኢንተርኔት አጠቃቀም መመሪያ በአማርኛ) የተባለው መጽሐፍ አዘጋጅ
No comments:
Post a Comment