በአስራ ስምንተኛው እና በ አስራ ዘጠነኛው መቶ ከ/ዘመን አካባቢ የኢንዱስትሪው
አብዮት መፈንዳት መላውን ዓለም በለውጥ ንቅናቂ አውድማ ላይ እንዳሰለፈው ሁሉ የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂውም ማደግ እና መዘመን የሃያ
አንደኛውን መቶ ክ/ዘመን ማህበረሰብ ከዳር እስከዳር በተሃድሶው ጎዳና ላይ እያንቀሳቀሰው ይገኛል፡፡ በትምህርት፣ በጤና ጥበቃው፣
በሳይንሱ፣ በጉዞወኪሎች፣ በህትመት ስራዎቻችን እና በመንግስት ተቋማት ዘንድ የሚሰሩ ባለሙያዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከኮምፒዩትር
አሰራር ጋር የተሳሰሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ አካሄዳቸውን ከግዜ ወደ ግዜ በማጎልበት ጥሶ በመውጣት ከፍተኛ ለውጥን አስመዝግበዋል፡፡
በሚቀጥሉት እርዕሶች የኮምፒዩትር ቴክኖሎጂው በዓለማችን እንዲት ልዩነቶችን በመፍጠር ላይ እንደሆነ እናያለን፡፡
ትምህርት
(Education)

ገንዘብ (Finance)
አያሌ ግለሰቦች
እና ድርጀቶች ንግዳቸውን ለማቀላጠፍ የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂውን ተጠቅመውበታል፡፡ ጥቂት የማይባሉ ሀገራዊ ሥነ ልክ (Standard)
ያላቸው ሶፍትዌሮች የሂሳብ ደረሰኞቻችንን ለመክፈል ገቢያችንን እና ወጪያችንን ለማሳወቅ ኢንቨስትመንታችንን ለመቆጣጠር የፋይናንስ
እቅዶቻችንን ለመገምገም ተጠቅመንባቸዋል፡፡ ለምሳሌ፡- አይቢኤክስ (IBEX) የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የገንዘብ ወጪዎች
መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ሲሆን ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ከሂሳብ ባለሙያዎቻቸው አስራር ጋር በመቀናጀት በሀሪቱ ውስጥ ላሉ የመንግስት
ተቋማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለ የቴከኖሎጂው አካል ነው፡፡ እንዲሁም አሲኩዳ የተባለውን የሶፍትዌር ፍርግም
(Program) የጉሙሩክ እና ገቢዎች ባለስልጣን ገቢ እና ወጭ ዕቃዎችን የገንዘብ ፍሰት ለመቆጣጠር ይጠቀምበታል፡፡
በቀጣዩ እየለሙ
(Developed) ያሉ እንደ IFMS ያሉ የወጪ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች በቀጥታ የአየር ላይ (online) ተጨማሪ አገልግሎቶችን
አካተዋል፡፡ ሀገር በቀል ባንኮቻችንም የኮር ባንኪንግ ቴከኖሎጂዎችን ተግባራዊ ማድረጋቸው ደንበኞቻቸውን በቀላሉ በያሉበት ቦታ ሆነው
የባንክ ሂሳባቸውን መቆጣጠር እንዲችሉ አግዟቸዋል፡፡ ያለደላሎች ጣልቃ ገብነትም የባንኮቻቸውን ትናንሽ ካርዶች ብቻ በመጠቀማቸው
የፈለጉትን ዕቃዎች መግዛትም ሆነ መሽጥ ችለዋል፡፡
መንግስት (Government)
መንግስት እንደተቋም
የመሀበረሰቡን የዕለት ዕለት እንቅስቃሴ ለማቀለጠፍ ከመቼውም ግዜ በበለጠ የመረጃ ሥርዓቱን እያገዘ እና እያሳደገ ይገኛል፡፡ ዜጎች
ወቅታዊ መረጃዎችን እንዲያገኙ ለመርዳት አያሌ የመንግት ተቋማት የራሳቸው የሆነ ድረ-ገጽ በመክፈት የመረጃ ልቀት የሚያካሂዱ ሲሆን
የታክስ ሂሳባቸውን በወቅቱ ለመሰብሰብ፤ የፍርድ ቤት ጉዳዮቻቸውን ለመጨረሰ የመብራት፣ የውሃ፣ እንደሁም የስልክ ወጪያቸውን ለመክፈል
በእጅጉ ተገልግለውበታል፡፡ በተያዘው የወደፊት አቅጣጫ መሰረት በሚቀጥሉት ዓመታት የቴኖሎጂውን አበርክቶት በማህበረሰቡ ውስጥ በእጥፍ
ለማስረጽ ከመሆኑም በተጨማሪ እያንዳንዱ ግለሰብ ወቅታዊ መረጃዎችን በአስፈላጊው ሰዓት እንዲያገኝ በር ከፍቶለታል፡፡
የጤና ጥበቃ Health CARE
የጤና ጥበቃ
መስጫ በሆኑ አካባቢዎች የኮምፒዩተር ቴከኖሎጂዎችን በእጅጉ መጠቀም ዉጤቱ ከፍተኛ እየሆነ መጥቷል፡፡ የቤተሰብዎን ሀኪም ለመጎብኘት ሲያስቡ ወይም ደግሞ ጤናዎትን ለማረጋገጥ ቢፈልጉ አልያም
የላብራቶሪ ምርመራ ቢያደርጉ እንዲሁም በደንገተኛ አደጋ ለተጐዱ ግለሰቦች በአፋጣኝ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል ቢገቡ ሀኪሞቻችን በሙሉ
በቴክኖሎጂው ሰነ ስርዓት ተከበው ተግባሮቻቸውን ሲያከናውኑ ያስተውላሉ፡፡
Ø ሆስፒታሎች እና ዶከተሮች የታካሚዎቻቸውን
መረጃ ለማጠናቀር የኮምፒዩተር እና ሞባይል ቴከኖሎጂዎችን በስፋት እየተጠቀሙበት ነው፡፡
Ø ትናንሽ ሮቦቶች የህክምና መሳሪያዎችን
በማቅረብ ነርሶችን እያገዙ ናቸው፡፡
Ø እነዚህ የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂዎች
ዶክተሮችን ነርሶችን በመርዳት የበሽተኛውን የህክምና ሂደት ሲያቃልሉ የታካሚውን የምርመራ ውጤትም በከፍተኛ ፍጥነት በመዘገብ የህመማቸውን
ስሚት እድሜ ለማሳጠር በቅተዋል፡፡
Ø የቀደ ጥገና ባለሙያዎች የጨረር
እና የልብ ቀዶ ጥገናዎችን በሚያደርጉበት ወቅት ከሮቦት ቴክኖሎጂዎች ከፍተኛ እገዛ ይደርግላቸዋል፡፡
Ø ከእነዚህም በተጨማሪ ቅጽበታዊውን
የተወያይ መድረክ (Chat) በመጠቀም ጥናታዊ ምርምሮቻቸውን ሊያሳድጉበት ተችሏቸዋል፡፡ በተለይም በዓለም ዙሪያ ካሉ የሙያ አጋሮቻቸው
ጋር ቴክኖሎጂውን በሁለት ዓይነት መንገድ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያው አንድ የህክምና ባለሙያ ባጋጠመው ህመምተኛ ዙሪያ
በሌላ ቦታ ካለ የሥራ ባልደረባው ጋር በመወያየት ልምድ የሚቀስምበት መፍትሄ ለመስጠት እውቀቶቹን የሚያዳብርበተ የቴከኖሎጂ ግብዓት
ሲሆን ቴሌሜዲስን በመባል ይታወቃል እንዲሁም ቴሌሴርጀሪን ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ የመተላለፊያ
ይዘት (Bandwidth) ያለውን አውታረመረብ (Network) አንዲሁም ከፍተኛ የማሳየት ብቃት ያላቸውን ካሜራዎች በመጠቀም በርቀት
ላይ ካለው የሙያ ባልደረባው ጋር በመተጋገዝ የቀዶ ጥገናውን የሚያከናውነበት የቴከኖሎጂ ሂደት ነው፡፡
ሳይንስ (Science)
ሁሉም የሳይንስ
ቅርንጫፎች የሚባሉት ከባዮሎጂ እስከ አስትሮሎጂ ከሜትሮሎጂ እስከ ጀኦሞርፎሎጂ ድረስ ያሉት የዕውቀት መስኮች የኮምፒዩተር ቴከተኖሎጂውን
መረጃዎችን ለመሰብሰብ እና ለመመዘን ይጠቀሙባቸዋል፡፡ ሳይንቲስቶች ጥናቶቻቸውን በተመለከተ ከቴክኖሎጂው በተጨማሪ ኢንተርኔትን ከሥራ
ጓደኞቻቸው ጋር እና ከተማሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘት እየተጠቀሙበት ነው፡፡
በ1973 ዓ.ም.
ዶክተር ማርቲን ኩፐር በእጅ የሚያዝ የሞባይል ስልክ እንዴት እንደሚሰራ ለማሳየት የመጀወሪያው ስወ ሆነ፡፡ እሳቸው የሰሩት ሞባይል
፡ የስልክ ባትሪ ፤ የራድዮ ማገድ መቀበያ እንዲሁም ማይክሮ ፕሮሰሰር የያዘ ትንሽ ኮምፒዩተር ነበረው፡፡ ዶ. ኩፐር በመንገድ ላይ
ሆነው በስልክ ሲነጋገሩ ሳለ የኒውዮርክ ነዋሪዎች አፋቸውን ከፍተው በአድናቆት ይመለከቶቸው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን መሳሪያ
ሊፈለስፉት የቻሉት ቀደም ሲል በ1800 አሌክሳንድሮ ቮልታ አስተማማኝ የሆነ ባትሪ ሰርቶ ስለነበረ ነው፡፡ በተጨማሪም ስልክ በ1876
ራዲዮ በ1895 እንዲሁም ኮምፒዩተር በ1949 ዓ.ም. ተፈልስፎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በ1971 ዓ.ም. ማይክሮ ፕሮሰሰር በመፈልሰፉ
የሞባይል ስልክ ሊሰራ ቻለ፡፡ እንደውም በአሁኑ ሰዓት ኮክሊያ የተባለውን የጆሮአችን ታምቡር በቴክኖሎጂው በመተካት መስማት ለተሳናቸው
ወገኖቻችን መስማት እንዲችሉ ሆኖአል፤ ረቲና የተባሉትን የዓይን ክፍሎችም ሙሉ በሙሉ በመለወጥ በጥቅም ላይ እየዋሉ ነው፡፡ በተጨማሪም
ትናንሽ ኮምፒዩተሮች የማዕከላዊውን የጭንቅላት የነርቨ ሲስተም በመኮረጅ እና ኤሌክትሮዶችን በጭንቅላት ውስጥ በመቅበር ፓርኪንስን
የተባለውን አንዘርዛሪ በሽታ ከሚያመጣው ተፅዕኖ መቋቋም ተችሏል፡፡ ካሜራ የያዙ ፒልሶችን አዘጋጅቶ ወደ ሰውነታችን በማስገባት ፓሊብስ፣
ካንሰርን እና ሌሎች አብኖርማሊቲዎችን በአይነቁራኛ መከታተል ቴክኖሎጂው የደረሰበት ተዓምር ነው፡፡
ህትመት (Publishing)
ህትመት ማለት
ቃላቶችን በማሰባጠ ትርጉም ሊሰጡ በሚችሉ መልኩ ለህብረተሰቡ መረጃዎችን ማቅረብ ነው፡፡ ይኸውም መጽሐፍት በማዘጋጀት፣ ጋዜጦችን
በመፃፍ፣ መጽሔቶችን፣ ሙዚቃ፣ ፊልም እና ቪዲዮዎችን አትሞ ማሰራጨት ይጨምራል፡፡ እነ አዶቤ ፎቶሾፕ የተለያዩ ግራፎችን በመሳል
እንዲሁም ገጾችን በማስዋብ ጽሁፎችን እና ምስሎችን (photo) በማሳመር ወደር የላቸውም፡፡
አርቲስቶች ሙዚቃቸውን
ለማቀናበር ፊልሞቻቸውን በመስራት ተወዳጅነትን ለመትረፍ ልዩ ልዩ የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ጋዜጠኞች እና የሞባይል
ተጠቃማዎች ገጠመኞቻቸውን በመቅረጽ እና በመዘገብ እንደ ፌስቡክ ባሉ የማህበረሰብ ድረ-ገጾች አማካኝነት ህዝባዊ ያደርጓቸዋል፡፡
አንዳንድ ግለሰቦች እና ሀገሮችም ጦማርን (Blog) እና እንደ ወኪፒዲያ ያሉ ወመዘክር ድረ-ገጾችን በመጠቀምም ታሪኮቻቸውን በመዘከር
ላይ ናቸው፡፡ ለወደፊትም ሙሉ በሙሉ የወረቀት ህትመቶች ቀርተው መረጃዎች በሙሉ ድረ ገጻዊ መሆናቸው አይቀሬ ነገር ነው፡፡
ጉዞ (Travel)
ከሪስቶፎር ኮሎምበስ
በ1449 ዓ.ም. አትላንቲክን ሲያቋርጥ ኮምፓስም ሆነ ምንም አይነት
አቅጣጫ ጠቋሚ ካርታ አልነበረውም በተጨማሪም ቪክስታንት የተባለው መሳሪያ እና ለባህር ላይ ጉዞ የሚያገለግል ክሮኖሜትር የተባለው
ሰዓት በ1730ዎቹ እስኪፈለሰፍ ድረስ የባህር ላይ ተጓዦች የሚገኙበትን ቦታ በትክክል መመልከት አይችሉም ነበር፡፡ በአሁኑ ግዜ
ግን በብዙ ሀገር የሚገኙ አሽከርካራች ከግሎባል ፖዚሽኒንግ ሲስተም
(GPS) ጋር ግንኙነት ባላቸው በጣም ውድ የማይባሉ መሳሪያዎች በመታገዝ መንገዳቸውን ማወቅ ይችላሉ፡፡ የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር
የምትሄዱበትን ቦታ በኮምፒዩተሩ ላይ መሙላት ብቻ ነው፡፡ ጉዞ አመላካች የሳተላይት መሳሪያዎች ሳተላይቱ የሚገኝበትን ግዜ እና ቦታ
ለአንድ ቢሊዮነኛ ሰከንድ እንኳን ዝንፍ በማይል ትክክለኝነት በማስተላለፍ እረገድ 24 በሚደርሱ ዝዋሪ የህዋው መርከቦች
(Satellites) ላይ የተመኩ ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያሉ የመኪና አምራች ካምፓኒዎች ኮንስታር የተባሉ አቀጣጫ ጠቋሚ ቴክኖሎጂዎች
በመኪናዎቻቸው ቦርድ ላይ እየገጠሙባቸው ሲሆን አብዛኛው ስማርት ፎኖች (Mobiles) ማለት ይቻላል አቅጣጫ ጠቋሚ የሆኑ ሪሲቨር
ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ በዚህ ላይ አነዚህን የስልክ ቀፎዎች ብቻ በመጠቀም ሰለሚሄዱበት ቦታ ሰለ ሚያድሩበት ሆቴል ስለሚከራዩት መኪና
እንደሁም ያለውጣ ውረድ በቀጥታ የጉዞ ትኬታቸውን መቁረጥ በመቻላቸው መንገዳቸው አልጋ በአልጋ ሆኖአል፡፡ እንግዲህ ምን ታስባላችሁ
ከቴክኖሎጂው ግብዓቶች ጋር አብሮ መራመድ መልካም አይመስላችሁም? ዓለም በስልጣኔ መረብ ላይ ቆሞ እያደረ የኛን ማንቀላፋት ምን
ይሉታል!!!
ሠላም ሁኑ
No comments:
Post a Comment