ሁለቱ ባላንጣዎች


የኢንተርኔት (በይነመረብ) አጠቃቀምን እና አገልግሎቱን የሚዘግበው መጽሐፍ ታትሞ ገብያ ላይ ከዋለ ቦኃላ ትንሽ የማይባሉ ተጠቃሚዎች ደውለውልኝ የነበር ሲሆን ከፍተኛ የመረጃ ምዝበራ እና ችግር እንደደረሰባቸው ገልጸውልኛል፡፡ የአብዛኛው ችግርም የያሁ ኢሜይል አድራሻቻው ባልታወቁ የኮምፒዩተር ቀበኞች እጅ መግባቱ እና የፌስቡክ አካውንታቸው መጭበርበር ነው፡፡
በተለይ የያሁ አካውንታቸው የተሰረቀባቸው በኢሜይል አድራሻቸው በኩል ሰማቸው ተጠቅሶ እና ችግር ላይ እንደሆኑ ተገልጾ የድረሱልኝ መልእክት የተላለፈባቸው በመሆኑ ከተለያዩ ጓደኞቻቸው እውነት ነው የሚለውን ለማረጋገጥ የስልክ ጥሪ ደርሶአቸዋል ይህ በእንዲህ እንዳለ ለብዙ አመታት የተለዋወጡአቸውን የፖስታ መልዕክቶቻቸውን እስከመጨረሻው አተዋቸዋል፡፡ እኔ በበኩሌ ላገኘዋቸው የኢሜይል ተጠቃሚዎች በሙሉ ጂ ሜይልን እንዲጠቀሙ የመከርኩ ከመሆኑም በተጨማሪ በመጽሐፋችን ላይም በስፋት ተተንትኖአል እናንተም ከሁለቱ ባላንጣዎች መካከል የተሻለ የሚያገለግለውን መርጣቸሁ ብትጠቀሙት ስንል እንመክራለን ጥበቃውን በተመለከተ ግን ጂሜይል ወደር አይገኝለትም፡፡ መልካም ንባብ፡-

ቅፅበታዊው የተወያይ መድረክ እና ኢሜይል (Integration of IM and Email)
በጣም ጠንካራ ከምንላቸው የቅፅበታዊ ተወያይ መድረኮች (Chat) አገልግሎት አኳ ጂ ሜይል የፖስታ አገልግሎት ተመራጩ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በቀላሉ እዛው የኤሌክትሮኒክ ሜሉ ውስጥ እንዳለን ቻት ለማድረግ ሳጥኑን መጠቀማችን ሲሆን የያሁ ሜይልን ያየነው እንደሆነ ግን ከኢሜይል አገልግሎቱ ተለይቶ በሚገኝ ሳጥን በኩል ለመጠቀም ሶፍትዌሩን መጫን ይኖርብናል ሰለዚህ ጂሜልን በዚህ ስራ አቅላይ አገልግሎቱ ልንመርጠው እንችላለን፡፡
ተያያዥ ፋይሎችን ማጣበቅ (Flexibility with Attachments)
በዚህም መልኩ ጂ ሜይል የተሻለ አገልግሎት ሰጪ ሆኖ እናገኘዋለን ምክንያቱም የጂሜይልን አገልግሎት እሰከ ተጠቀምን ድረስ የትኛውም ያህል ብዛት ያላቸውን ተጣባቂ ፋይሎች ልናያይዝበት እንችላለን ያሁን የተመለከትን እንደሆነ ግን በአንድ እስክሪን ላይ ብቻ ከ 5 ያልበለጡ ተያያዥ ፋይሎችን ብቻ እኛጣብቅበታለን ተጨማሪ ማያያዝ የፈለግን እንደሆነ ግን ሌላ ተጨማሪ እስክሪን መጠቀም ይኖርብናል፡፡
የአቃፊዎች አደረጃጀት (Folder Organization)
በተለምዶ የፎልደር አደራደራቸውን በተመለከተ ያሁ የተሻለ ይዘት ይኖረዋል ምክንያቱም እንድ ተጠቃሚ የያሁን የፖስታ አገልግሎት እስከተጠቀመ ድረስ በፈለገው መልኩ የገቢ መልዕክቶቹን (Inbox) ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ መረጃዎቹን መለያ ስም (label) እየሰጠ ደርድሮ ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ጂሜይልን የተመለከትን እንደሆነ ግን ያሉንን የፋይል አቃፊዎች  (Folders)  በተመሳሳይ ቦታዎች ያስቀምጣቸዋል ይህውም ፋይሎቻችን እና ፎልደሮቻችን እየበዙ በመጡ ቁጥር እንዱን ከአንዱ በቀላሉ ለመለየት እንቸገራለን፡፡
የተያያዥ ፋይለች መጠን (Size of Attachments)
ሌላው የጂሜይል ምርጥ ይዘቱ የምንልከው የተያያዥ ፋይል መጠን ብዛት ሲሆን የጂሜይል ፖስታ አገልግሎት በቀላሉ እስከ 20ሜጋ ባይት የሚደርስ መጠን ያለው ፋይል በቀላሉ እንድናዘዋውር የሚፈቅድልን ሲሆን የያሁ ሜይልን የተመለከትን እንደሆነ ግን ከ 10 ሜጋባይት የበለጠ ፋይሎችን አያይዘን ልንልክበት እልችም፡፡
የአገልግሎት ጥራት ተፅኖ (Brand Impact)
ሌላው የጂሜይል ጥራት የአገልግሎቱ ታዋቂነት ሲሆን ከያሁ በተሻለ መልኩ ዘመናዊነትን የተላበሰ እና ያለጥርጥር የሰለጠነ አገልግሎት ሰጭ ኤሌክትሮኒካዊ የፖስታዎች መላላኪያ (E-mail service) ነው፡፡
 ታዲያ ማነው ተመራጩ? (So who’s the winner?)
 መልሱ ያለጥርጥር ጂ ሜይልነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት አገልግሎቶቹ ብቻ እንድን መርጠው ያደርገናል በተለይ አገልግሎት አሰጣጡ ሙያዊ በመሆኑ እና በጣም ዝነኛ ሚስጢር ጠባቂ በመሆኑ ልንተማመንበት ይገባል፡፡ በመጽሐፋችን ላይ እንደተቀመጠው ( በይነመረብ page 43) የሁለተኛውን አማራጭ (Tow Step Verification) አገልግሎት መጠቀማችን የበለጠ በፖስታ መልእክቶቻችን ጥባቆት እንድንተማመን የሚያደርገን ከመሆኑም ሌላ በገዛ ሀገራችን ቋንቋ እንድንጠቀምበት የሚደርግ በመሆኑ አንዳች ውበት አለው፡፡

No comments: