በይነመረብ
የኢንተርኔት አጠቃቀም መመሪያ
በአማርኛ የተባለው መጽሐፍ
ተጽፎ ለህዝብ አገልግሎት
ጥቅም ላይ ከዋለ
ቦኃላ ትንሽ የማይባሉ
የመጽሐፉ አንባቢዎች የቴክኖሎጂውን አጠቃቀም
በተመለከተ የቤት ለቤት
ስልጠና እንድንሰጣቸው ጠይቀውናል፡፡
- ቴክኖሎጂውን የመጠቀም ጉጉቱ ኑሯቸው ትምህርት ቤት ገብቶ ለመማር ግዜውን ያጡ፡፡ታዋቂ ሰዎች ሆነው የቴክኖሎጂውን ውስጣዊ አሰራር የበለጠ ለመረዳት ግዜ ያጠራቸው፡
- እንደማንኛውም መደበኛ ትምህርት የራሱ ክፍለ ግዜ የሌለው ሰለሆነ በኢንትርኔት አጠቃቀሙ ዙሪያ በቂ እውቀት ያልጨበጡ፡
- እንደማንኛውም የቴክኖሎጂ ሰው ክፍለ ዘመኑን በብልጥት እና በእውቀት ለመቆጣጠር የሚፈልጉ፡
- የድርጅቶቻቸውን እና የንግዶቻቸውን አሰራር ከቴክኖሎጂው ጋር ለማዋደድ የሚሹ፡
- ልጆቻቸው ሰለ እንተርኔት አጠቃቀም በሚገባ ማወቃቸው በትምህርታቸው ሆነ በስነምግባራቸው ላይ ለውጥ ያመጣል ብለው የተገነዘቡ ታዋቂ ሰዎች፣ ነጋዴዎች፣ ግለሰቦች፣ ተማሪዎች፣ ድርጅቶች፣ ወዘተ ስማቸውን እና አድራሻችውን ጠቅሰው በስልክ እና በ ኢሜይል አድራሻችን የተለያዩ መልእክቶችን አስተላለፈውልናል፡ ከዚህ በመነሳት ጉዳዩን ስናስብበት ከቆየን ቦኃላ እንደየአስፈላጊነቱ ለተግባራዊነቱ እቅድ አውጥተን እንቅስቃሴ ጀምረናል እርስዎም የእቅዱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጋብዛለን፡፡ ይደውሉልን 0912153087
No comments:
Post a Comment