በሃገራችን ውስጥ ባለ አንድ አሃዝ ኢኮኖሚ (Monopolistic
Economy) ከሚጠቀሙ
ካምፓኒዎች
መካከል
አንዱ
ቴሌኮም
ነው፡፡
ይህውም
ከኃላ
ቀር
ከአሰራሩ
እንዳይማር
እና
በገብያ
ተወዳድሮ
እንዳያሽንፍ፤
ደግሞም
የተሻሉ
የቴክኖሎጂ
ግብዓቶችንም
በአግባቡ
እንዳይጠቀምባቸው
አዘናግቶታል፡፡
ካምፓኒው
ከፍተኛ
የገንዘብ
መጠን
ከህብረተሰቡ
እንደሚያጋብስ
ቢታወቅም
የቢሮዎቹን
ቁጥር
ከማብዛት
እና
ኔትውኩን
ከማጨናነቅ
ውጪ
የፈየደው
ነገር
የለም፡፡
ምክንያቱ ብዙ በመሆኑ መፍትሄ ለማግኘት ወደ ካምፓኒው መጉረፍ የተለመደ ነው፡፡ ድርጅቱ በሙስና ከመጨማለቁም ባሻገር በየግዜው የሚገዙት የቴክኖሎጂ እቃዎች ፎርጅድ በመሆናቸው ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፡፡ መብራት ኃይል ደግሞ የበለጠ ችግሩን ቤንዚል እያርከፈከፈበት ነው፡፡ ለመሆኑ በየወሩ ለሞባይል ካርድ እየተባለ የምታወጡትን የገንዘብ መጠን ታውቁታላቸሁ? የኔትወርክ ቴክኖሎጂው አያደገ በመጣበት ዘመን የኛው ቴሌኮም እንደቀንድ አውጣ መንቀራፈፍ ምን ይሉታል! እኔ በበኩሌ መሮኛል!፡፡

ለመሆኑ ቮይስ ኦቨር አይፒ ምንድን ነው?
ቮይስ ኦቨር አይፒ ማለት የኢንተርኔት ህጎችን በመጠቀም መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል ሥነ ልክ (Standard) ሲሆን ሃገራችን ላይ በስፋት የሚታወቀው የኢንተረኔት ስልክ በመባል ነው፡፡ ይህው ሥነ ልክ በጊዜዎች ሂደት ስካይፕ፣ ኒምቡዝ፣ ቫይበር ወዘተ የተባሉ ህጉን መተግበሬያ የሶፍትዌር ፍርግሞች (Program) ወልዶአል፡፡
ቴክኖሎጂው ከጥቂት ወራት በፊት የተፈቀደ በሚመስል መልኩ መግለጫ የተሰጠበት ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግራ መጋባቶችን እያስተናገደ ነው፡፡ የቴሌኮም ፍፃሜ እሩቅ ሰለማይሆን ቀብሩን ለማሳመር ከመሯሯጥ
ይልቅ የፈጠራ ሰዎችን
ለማብቃት ጥረት ቢያደርግ መልካም ነበር፡፡
ይሁን እንጂ የመረጃዎች ኬላ ተብሎ በይፋ ከተቋቋመው የመንግስት ቢሮ ወይም ኢንሳ ጋር በመሆን ድረገ ጾችን እና ጠቃሚ ሳይቶችን ለመዝጋት በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ከመመደብ መቶሺዎችን አውጥቶ ፈጠራዎችን ቢያበረታታ የት በደረሰ፡፡
እንግዲህ ማህበረሰቡ የበለጠ የዘመናዊ ስልኮች ተጠቃሚ እየሆነ በመጣ ቁጥር ቴሌኮም ያለአግባብ የሚቸበችባቸው የሞባይል ካርዶች አንድም ተጠቃሚ ሰለማይኖራቸው አንድም ጥራት ሰለሚጎላቸው ቴሌኮም ሦስት ነገሮችን ሊያደርግ ይገደድ ይሆናል አንደኛው የመረጃ ስርዓቱን በማንቀራፈፍ እና በመበጣጠስ ሶፍትዎሮችን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ሲሆን አሁን እየተደረገ ያለውን ልብ ይሏል ምክንያቱም የድምጽ እና የምስል መረጃዎችን በጥራት ለማስተላለፍ የኔትወርኩን አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ማንቀራፈፍ ለግዜው ቢጠቅመውም ለወደፊቱ ግን አያዛልቀውም ምክንያቱ ደግሞ በቀጥታ ከሳተላይት ጋር የሚሰሩ የሞባይል ቀፎዎች እየተመረቱ በመሆናቸው ነው አዲዮስ ቴሌኮም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ግልጽ ማስፈራሪያዎችን በጽሑፍ መልዕክቶች በመላክ መዛት ሲሆን ይሄኛውም አካሄድ የሚያዋጣው አይሆንም ምክንያቱ ደግሞ ኬሌሎች ሃገር ካምፓኒዎች በግልጽ መማር ሰለሚኖርበት ነው፡፡ ሦስተኛው ግን ከዚህም ባስ ይላል ምክንያቱም እያንዳንዱ የስልክ ጥሪዎች፣ ድረ ገጾች ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶች በሙሉ ኢንሳ በተባለው የስለላ መረብ ወደተጠቃሚው ከመሄዳቸው በፊት መበርበር ሰለሚኖርባቸው ነው፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከውጭ የሚደወሉ ስልኮች 0937000000 ወደሚል ይዘት መቀየራቸው እየተሰለልን መሆኑን የሚናገር አይን ያወጣ ድርቀት ነው፡፡ እንደውም
ኢትዮጵያ
ከጥቂት
ዓመት
ወዲህ
የመረጃ
ሥርዓቱን
በማገድ
ከዓለም
ሃገራት
በሁለተኛነት
ተፈርጃለች፡፡ የቮይስ ኦቨር አይፒን ሥነ ልክ ተጠቅሞ ብዙ የገቢምንጮችን ማዳበር እንደሚችል ቴሌኮም ማሰብ ነበረበት ነገር ግን ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር እንቅልፋም ስለሆነ ለውጡ አይታየውም የኔትወርክ መጠኑ ያነሰው የሰው ቁጥር ሰለበዛ ነው ብሎ ሲፎግረን ትንሽ አይሰቀጥጠውም! እንዴት በአንድ ሳምንት ውስጥ የኔትወርክ መስመሩ ይህን ያህል ሊጣበብ ይችላል ደግሞስ ሲምካርድ ከመቸብቸብ ይልቅ አስቀድሞ ኔትወርኩን ማስፋፋት አይቀድምም በእርግጥ በየግዜው በርካሽ ዋጋ የሚቸበቸቡት የቴክኖሎጂ እቃዎች ጥራት ይጎላቸዋል፤ በፎቆች ምክንያት ነው የተባለውስ አሳማኝ ነው? የትኞቹ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ተሰርተው ነው ኔትወርኩ አልሰራም ያለው? ዱባይ ቴሌኮም ካምፓኒዎች እንኳን እንደዚህ አላሉም፡፡ ባይሆን በየቦታው የተከልናቸው መሳሪያዎች ፎርጅዶች በመሆናቸው ሞገዱን ለማሰራጨት አቅም ሰለሌላቸው ነው ብትሉ ምክንያታዊ ይሆን ነበር፡፡ ገንዘብ ለማጋበስ ከመሮጥ ኔትውኩን ለማሮጥ መጣር ሃገራዊነትን ያሳያል!
No comments:
Post a Comment