ጂፒኤስ (GPS/Global
Positioning Systems
) ምድር ላይ ተተካይ በሆኑ የሞገድ መቀበያ አንቴናዎች
በመታገዝ ጂኦግራፊያዊ አቅጣጫዎችን የሚጠቁሙ ተንቀሳቃሽ የህዋው ላይ መርከቦች
ሲሆኑ መረጃውን ለማሳለጥ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ 24 የሚሆኑ ሳተላይቶችን ይጠቀማሉ፡፡ የጂፒኤሱን መረጃ ለመቀበል እዲችሉ በአሁን
ሰዓት እየተመረቱ ያሉ ሞባይል ቀፎዎቻችን፣ መኪኖቻችን እንዲሁም ሌሎች የኤሌክተሮኒክስ መሳሪያዎቻችን ተለጣፊ ወይም ድብቅ (Embedded)
አንቴናዎች የሚገጠምላቸው ሲሆን ያሉበትን ለመጠቆም እንዲረዳ የምስል ማሳያ (Screens) ተገጥሞላቸዋል፡፡ ጥቂት የተንቀሳቃሽ
መሳሪያዎች ምስሎችን ለመቃኘት እና ሙዚቃን ለመኮምኮም የሚስችል ብቃት አላቸው (iPod)፡፡ አባዛኛው የሞባይል ቀፎዎች ደግሞ የጂፒኤሶችን
ሞገድ (Signal) መቀበል (receiver) የሚያስችል ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማሉ (such as smart phones, automobile, boat, airplane, farm and construction
equipment, or computer)፡፡ የሳተላይቶቹ ዋና አላማ ለዓለም ህዝብ ትክክለኛ
የሆነ የቦታ ጥቆማ መስጠት ሲሆን የተለያዩ ቦታዎችን ለመጠቆም፣ የጠፉ ሰዎችን ወይም እቃዎችን ለመፈለግ፣ የሰዎችን ቅስቃሴ ለመቆጣጠር፣
የቦታዎችን ከፍታ (Altitude) እንዲሁም ፍጥነትን ለመለካት ያገለግላሉ፡፡
አያሌ ተሸከርካሪዎች መንገዶችን ለመጠቆም እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጂፒኤስ
የተባሉትን መሳሪያዎቸ ይጠቀሙባቸዋል ለምሳሌ የተራፊክ ፍሰቱን፣ ቅፅበታዊ የመኪና አደጋዎችን ለመጠቆም፣ የመንገድ ላይ ብልሽቶችን
ለመፍታት፣ የመኪና ቁልፎች ተረስተው ሲቆለፍባቸው እንዲሁም የመኪና ስርቆቶችን ለመከላከል ይረዳሉ፡፡ እንደውም አዳዲሶቹ የጂፒኤስ
ተጠቃሚ ማሳሪያዎች በአጠገባቸው ያለን ነዳጅ ማደያ፣ መዝናኛዎች፣ ሆቴሎች፣ በተጨማሪም በርቀት ካለው ድርጅታቸው የአጋጣሚ አደጋ
እርዳታ ሁሉ ይጠይቃሉ፡፡ አባዛኛው የሞባይል ገመድ አልባ ሞገዶች ከቴክኖሎጂው ጋር የተገናኘ በመሆኑ የቤተሰብ አባላት ልጆቻቸውን
በቀላሉ የት ቦታ እንዳሉ ለመጠቆም ተችሏቸዋል፡፡
2 comments:
በጣም አሪፊ ጅማሮ ነው ትልቅ ጦማር እንደሚወጣው አልጣራጠርም
እየሰጣችሁን የለው መረጃ እጅግ በጣም የሚበረታታ ነው፡፡ በርቱ
Post a Comment