ዲጄ
ሊ አርብ ምሽት ኤፍ ኤም 97.1 ላይ ላስተላለፈችው የተሳሳተ መረጃ የተሰጠ እርምት!!!
አጅግ በጣም አስቃቸሁናል ምክንያቱም ሻይቡናን ድረ ገጽ ከፌስቡክ፤ ድሬ ትዩብን ደግሞ ከዩትዩብ ጋር ለማመሳሰል መሞከራቸሁ የማይታመን ነው፡፡ ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ አለ ያገሬ ሰው! በሃገሬ የድረ ገጽ ልማት እድገት ላይ ኩራቴ ከፍተኛ ቢሆንም እንደው ከመሬት ተነስተን ከዓለም ዓቀፉ የማህበረሰብ ድረ ገጽ ጋር ለማወዳደር መሞከሩ አግባብ አይመስለኝም፡፡ ምን አልባት ዝግጅታችሁን ስፖንሰር ለማድረግ የከፈሉት ገንዘብ መጠን ከፍተኛ ሆኖ ነገርየውን ከፌስቡክ ጋር ለማወዳደር አኳሽቶአችሁ ከሆነ አልፈርድባችሁም ገንዘብ ነው እና ቢዝነሳችሁን ወድጄዋለው፡፡ ይሁን እንጂ እውነታው ሁለት ነገር ላይ ይወድቃል የመጀመሪያዉ ሰለምታወሩት ነገሮች በቂ እውቀት የሌላቸሁ መሆኑ ሲሆን ሌላው ደግሞ ፌስቡክን በደንብ ጠልቃችሁ አለመጠቀማችሁ ነው፡፡ ለምሳሌ ፒያሳ ላይ ሆኜ ሜክሲኮ ላይ ሳልዘጋው የተውኩትን የፌስቡክ አካውንት መዝጋት አንደምችል ታውቃላቸሁ? ራሱን ከቫይረሶች እና ተመሳሳይ የበይነመረብ ላይ ተውሳኮች እንደሚከላከልስ? አንደውም እንደ ኢሜይል አድራሻ ሁሉ ራሱን ችሎ የኢሜይል አገልግሎት የሚሰጠ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፣ የመያዝ አቅሙስ ቢሆን እስከ 1000 ሺህ ፎቶዎችን ልታጭቁበት እንደምትችሉ አስቡት ምን ያህል ቦታ እንደሚያስፈልገን? ይህንን ያህል ቢሊየን ህዝብ ሊያስተናግድ መቻሉስ! ሻይቡና ይቅር እና ቴሌኮም እንኳን ይህን ያህል ድር አስተናጋጅ (web server) ማሽኖች የሉትም ምን አልባት በሀገራችን ቋንቋ የሚዘግብ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባል ግን እኮ እናንተ ዝቅ ያደረጋችሁት የዩትዩብ ባለቤት የሆነው ጉግል ካምፓኒ በአማረኛ፣ ትግረኛ፣ ኦሮማኛ፣ ሱማሌኛ፣ አፋረኛ የሚዘግብ መሆኑ መዘንጋት የለበትም እንደውም አብዛኛዎቹ የሀገር ውስጥ ድረ ገጾች ጽሁፎቻቸውን ለማዘመን (update) ሲፈልጉ የሚጠቀሙት አገልግሎት የጉግል እንጂ እራሳቸው የፈጠሩት አለመሆኑን ልብ ማለት ይኖርብናል፡፡ ታዲያ በምን ሂሳብ ነው ሻይቡና ዶት ኮም ከፌስቡክ፤ ድሬ ትዩብ ደግሞ ከዩትዩብ ጋር ሊወዳደር የሚችለው፡፡ አኔ በበኩሌ አሳፍሮኛል ሆኖም ሻይቡናም ሆነ ድሬ ትዩብ በርቱ፣ ተመንደጉ፣ ዘምኑ ሊባሉ ይገባል፡፡ የማይመሳሰሉ ነገሮችን ለማመሳሰል መሞከሩ ግን እውነታውን መካድ ነው እና ይቅርብን፡፡ ይልቁንስ ሁሉም ድረ ገጾች የየራሳቸው የሆነ ውበት ስላላቸው ውበታቸውን ይዘው አንዲቀጥሉ ብናበረታታቸው መልክም ነው፡፡ http://www.shaybuna.com/
No comments:
Post a Comment