ጥርስ እንደ ኪቦርድ



በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከአንገታቸው ጀምሮ እሰከ ጀርባ አጥንታቸው ድረስ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው እንደልብ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ከቴክኖሎጂው እርቀው ተቀምጠዋል፡፡ ነገር ግን ከወደ ጆርጂያ አካባቢ የተሰማው ዜና ብዙዎችን ያስፈነደቀ ከመሆኑም ሌላ የጀርባ አጥንት ተጎጂዎች በምላሳቸው አማካኝነት ቴከተኖሎጂውን መቆጣጠር ችለዋል ምክንያቱም የምላሳችንን ክፍል የሚቆጣጠረው ክራኒያል ነርቭ በመሆኑ ነው፡፡ ለእነዚህ የአካል ጉዳተኞች የጆርጂያ ቴክኖሎጂ ኢኒስትትዩት አሪፍ ዜና ይዞ ብቅ ብሎአል ይህውም ምላስን እንደ አስገቢ መሳሪያዎች (Input Device) መጠቀም ነው፡፡  በጆርጂያ ቴክኖሎጂ ኢንስትትዩት ውስጥ ምላስ እንደ ጆይሰቲክ ያገለግላል ሲባል ማሰገረሙ አልቀረም፡፡ ይህ እጅግ በጣም ትንሽ ማግኔቲክ መሳሪያ በምላሳቸው ጫፍ ላይ በቀዶጥገና የተቀበረ ሲሆን ሰውየው ምላሱን ማንቀሳቀስ ሲጀምር ሴንሰሩ የማግኔቱን እንቅስቃሴ በመከታተል በ6ቱም አቅጣጫ እያንዳንዱን ነገር ይቆጣጠራል፡፡ መሳሪያው መልዕክቶችን ሲልክም (send) መልዕክቱን ለመቀበል (receiver) እንዲቻለው ተጠቃሚው እራስ ላይ የታሰረ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ሲሆን በቀላሉ የኮምፒዩተሩ መገልገያ መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር ያስችለዋል፡፡ ለምሳሌ ሰውየው የሚጠቀምበትን ዊልቸር ወደ ኃላ ለማስኬድ ቢፈልግ ምላሱን ወደኃላ በመቆልመም ብቻ ወደኃላ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ይችላል እንዲሁ ወደግራ (left) ወደቀኝ (right) ወደፊት አንደልብ መንቀሳቀስ ተችሏል፡፡ ምን ይሄ ብቻ አንድ ግዜ ጠቅ (Click) ፣ ሁለት ግዜ ጠቅ (Double Click) ለማድረግም መላሱን መጠቀም ብቻ በቂ ነው፡፡ እንደውም ኢንስቲትዩቱ ለወደፊት የሚያስበው እያንዳንዱ ጥርሳችንን እነደመፃፊያ ሰሌዳው (Keyboard) ለመጠቀም ነው፡፡

No comments: