ቲሲፒ/አይፒ



ሁልግዜም ኮምፒዩተሮቻችን በበይነመረብ ኔትወርክ ገመድ ውስጥ እስከገቡ ድረስ ለራሳቸው ቋሚ ወይም ቋሚ ያልሆነ (DHCP) መገልገያ ቁጥር ይኖራቸዋል ይህውም ቲሲፒ/አይፒ (TCP/IP) በመባል ይታወቃል፡፡ እያንዳንዱ መረጃ በኢንተርኔት ውስጥ በሚያልፍበት ወቅት የኮምፒዩተሩን የአይፒ አድራሻ የሚይዝ ሲሆን ለመላክ ተብሎ የተፈጠረውን መረጃ ይወክላል፡፡ በመካከል ያሉ ማዞሪያዎች (Routers) ይህንን አድራሻ በመጠቀም የመጡትን ፓኬቶች ወደ የትኛው አቅጣጫ መተላለፍ እንደሚገባቸው ይወስናሉ፡፡
ተጠቃሚዎች ይህንን የአይፒ አድራሻ በቀጥታ መፃፍም ሆነ መመልከት አይጠበቅባቸውም ሞንክያቱም እያንዳንዱ ኮምፒዩተር የራሱ የሆነ የጎራ ስም (Domain Name) በራሳቸው ግዜ (Automatically) የሚሰጡ ሲሆን የፕሮቶኮል ሶፍትዌሮች ደግሞ ይህንን ተከትለው የአይፒ አድራሻ ይሰጡታል፡፡ ቀለል ለማድረግ ሶፍትዌሮቹ የጎራ ስሞችን ወደ አይፒ አድራሻ ይቀይሩለታል፡፡




No comments: