ወላጆች ስለፌስቡክ እንደ ወላጅነት ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች

ወላጆች ለበይነመረቡ (Internet) ዓለም በልጆቻቸው ህይወት ላይ ቁልፍ ሚና መጫወት አለባቸው፡፡ ልጆቻቸው ጥሩ የሆነ የራስ መገለጫ እንዲኖራቸው፣ ጥሩ ግኑኝነትን እንዲመሰርቱ እና የማህበራዊ ድረ ገጽን በመጠቀም ቀና የሆነ ስእብና ማትረፍ እንደሚችሉ ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡ ለወላጆች ይጠቅማል ከሚባሉት የማህበረሰብ ድረ ገጽ አጠቃቀም መመሪያዎች ውስጥ ጥቂት ልበል፡
• የፌስቡክ ጥቅም ፍጹም ለግል ነው፡- ለዚህም ነው የመጀመሪያው የጥንቃቄ መርህ “ከልጆችዎ ጋር ይነጋገሩ” የሚለው፡፡ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ለመነጋገርት የማህበራዊ ድረ ገፅ አዋቂ ወይም ሊቅ መሆን አይጠበቅባቸውም፡፡ ለምሳሌ፡- ለምን ፌስቡክን መጠቀም እንደፈለጉ በመጠየቅ፣ የጊዜ ሰሌዳቸው ላይ ምን ምን ማካተት እንደሚችሉ እንዲያሳዩቻችሁ ማድረግ፣ የትኞችቹ አይነት መረጃዎች በማህበረሰብ ድረ ገፅ ብንለቅ/ብናካፍል ተገቢ ይሆናል ወይም ተገቢ ያልሆኑት የትኞቹ ናቸው ወ.ዘ.ተ የሚሉት ከልጆችዎ ጋር ጥሩ መነሻ መነጋገሪያ ነጥቦች ናቸው፡፡
• እንደወላጅነትዎ የመፍትሔም አካል ነዎት፡- ምንም አይነት መጥፎ ነገር ቢከሰት ሊነገርዎት ይገባል፡፡ ስለፌስቡክ ወይንም ስለሌላ የማህበረሰብ ድረ ገጽ ብቻ አይደለም በተለይ ልጆችዎ የበይነመረብ (Internet) አጠቃቀማቸው ምን እንደሚመስል፤ የእርስዎን እርዳታ ይፈልጋሉና፡፡
• ምንም ዓይነት መጥፎ ነገር ቢከሰት ላለመቆጣት ይሞክሩ፡ ለእርስዎ እንዲነገርዎ እና የመፍትሔ አካል ለመሆን እንዲችሉ ይረጋጉ! ልጆች ወደ ወላጆቻቸው ለመሄድ እና ለማማከር የሚደፍሩት ከወላጆቻቸው ጋር የሚያደርጉት ንግግር እረጋ ባለ እና አሳቢነት በተሞላበት መንፈስ እንደሆነ ይወቁ፡፡ በይበልጥ ሊረዱዋቸው የሚችሉት ልጆችዎ እርስዎን ለማናገር የመረጡ እንደሆነ ብቻ ነዉ፡፡ ስለዚህ ከእርስዎ ጋር እንዲነጋገሩና እንዲረዷቸው ያለውን እድል ያሰፋሉ፡፡
• በአሁን ጊዜ እየተለመደ የመጣውን የተጠናከረ ቤተሰባዊ መመሪያዎችን መጠቀም (The well stocked toolbox of today’s parenting)፡ በቤተሰብ ውስጥ ዋጋ የሚሰጠውን ወይንም መከበር ያለባቸውን ህጎች በደንብ ማጠናከር፤ የቤተሰብ ህግንና መመሪያ ማውጣት፤ ለምሳሌ የኢንተርኔት መጠቀሚያን በግዜ ሰሌዳ ተግባራዊ ማድረግ፡፡ አንዳንዴም የወላጆች መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን ወይንም ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፡፡ ወላጆች እነዚህን መሣሪያዎች እየተጠቀሙ ከሆነ ለልጆችዎ የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች እየተጠቀሙ መሆኑን መናገር እንዳለባቸው ይመከራል፡፡
• ሌሎችን ለወላጆች ጠቃሚ የሚሆኑ ምክሮችንም በ https://www.facebook.com/safety/groups/parents/ ፌስቡክ አድራሻ ታገኛላችሁ፡፡

No comments: