ድረ ጦማር

ድረ ጦማር በአጭሩ ጦማር (web log or Blog) በአውደ መረባችን (WWW) ውስጥ እንደ መፅሔት፣ የዕለት ማስታወሻ ገጠመኞቻችንን መፃፍያ (Diary) እንዲሁም አስተሳሰባችንን ለሌሎች የምናካፍልበት ሥርዓተ መረብ ሲሆን እራሱን ችሎ ያልቆመ ነገር ግን የአሰራሩ ሁኔታ ከመደበኞቹ የመካነ ዳሮች (web site) ጋር የሚመሳሰል የጥሞራ መድረክ ነው፡፡
ጋዜጠኞች፣ ዘፋኞች፣ መለስተኛ የግል ተቋማት፣ መምህራን እንዲሁም ግለሰቦች ሳይቀር የዕለት ዕለት እንቅስቃሴቸውን ሂደት በማጋራት ከማህበረሰቡ ጋር ሊገናኙበት ይችላሉ፡፡ በዚህ የጥሞራ መድረክ ላይ የሚስተናገዱ ጽሑፍ ነክ ማስታወሻዎች ግዚያቸውን ጠብቀው የሚደረደሩ (Chronological order) ሲሆን ምናልባትን ምስልን ጨምሮ የሚያጋሩ ከሆነ ደግሞ የምስል ጦማር (V Log) በመባል ይታወቃሉ፡፡ ሌላው ጥቅነ ጦማር (Micro Blog) የምንለው ሲሆን ከመቶ እስከ ሁለት መቶ ድረስ ባሉ ቃላት ብቻ በመጠቀም ሃሳባችንን የምናካፍልበት መድረክ ነው፡፡ ትዊተር የተባለው ብሎግ ለዚህ ዋና ተጠቃሽ ሊሆን ይችላል፡፡ ቀሪውን መጽሐፉ ላይ ያገኙታል

No comments: