የአውታረመረብ (Network) ዘበኞች


ቦትኔት እርስ በራሳቸው ተሰማምተው እና ተግባብተው ከኔትወርኩ ጋር የሚሰሩ ኮምፒዩተሮች ሲሆኑ የራሳቸው ወደ አልሆነ የኔትወርክ ዝርጋታ በመግባት መሰሪ የሆነ ጥቃቶችን ይሰነዝራሉ፡፡ እነዚህ ተመቻማች (compromised) ኮምፒዩተሮች ዞምቢ በመባል የሚታወቁ ሲሆን ተጠቃሚው ግለሰብ ባልተረዳው መልኩ ወደ ሲስተሙ በመግባት መረጃዎቹን በሙሉ ከሌላ ቦታ ሆነው ይቆጣጠሩታል፡፡ ቦት የሚባሉት በኔትውርክ መስመሩ ውስጥ ተደጋጋሚ ህገውጥ ስራዎችን የሚሰሩ የፕሮግራም ዓይነቶች ሲሆኑ ዓለመ ወንጀለኞች (Cyber criminals) በኔትወርክ መስመሩ ውስጥ እራሱን ባልጠበቀ የኮምፒዩተር (unprotected computers) ሲስተም ላይ ቦትኔት የተባሉትን ፕሮግራሞች በመጫን ዞምቢ አርሚዎችን ይፈጥራሉ ከዛ ቦኃላማ በቃ የግለሰቡን መረጃ በመስረቅ፣ ስፓሞችን በኢሜይል ሳጥን ውስጥ በመላክ፣ ቫይረሶችን እና ማልዌሮችን በማሰራጨት፣ እየተጠቀማቸው ያሉ እገልጋይ ሶፍትዌሮችን በመምታት ከፍተኛ ጉዳት ያደርሱባቸዋል፡፡ ታዲያ መጠንቀቅ አስፈላጊ አይመስልህም? የአውታረመረብ (Network) ዘበኞችን /ኬላ (Firewall) በአግባቡ መጠቀም ሊመጣ ካለው ጥቃት የሚታደጉ ፍቱን ምሽጎች ናቸው::

No comments: